በአዲስ
አበባ በተለምዶ አራዳ ጊዮርጊስ እየተባለ በሚጠራው ቤተክርስትያን አከባቢ ጀምሮ እስከ አትክልት ተራ ድረስ በቀላል የባቡር ጣብያ
መስፋፍያ ምክንያት በቆርቆሮ ታጥሯል፡፡እናም ከምንሊክ አደባባይ ወደ ቤተክርስትያኑ አከባቢ ያሚያዘልቀው መንገድ በመንገደኞች ከልክ
በላይ በመጨናነቁ ለማለፍ ሰልፍ፣ ግፍያ መታገል ያስፈልጋል፡፡
ታክሲና ባስ ለመሳፈር፣ዳቦ ለመግዛት፣ኮንደምኔም ቤት ለመመዝገብ፣ የባንክ አካውንት
ለመክፈት፣ብር ለመቆጠብ፣የቆጠቡትን ብር ለማውጣት … ሰልፍ ያስፈልጋል፤ የተለመደ ነው፡፡ አሁን ግን ይባስ ብሎ በእግር ለመጓዝም
ሰልፍና ግፍያ የግድ እየሆኑ ነው፡፡እንዳውም የሰይጣን ጀሮ ይደፈንና ለእግረኞችም የትራፊክ መብራትና ፖሊስ ሳያስፈልግ አይቀርም፡፡
ስልክ
ለመደወል ቢያስፈልጎ ‹‹መስመሮቹ ሁሉ ተይዟል፤ እባክዎ ትንሽ ይጠብቁ›› ይባላሉ፡፡
የEVDO ፍጥነት ከCDMA
1X በታች በመሆኑ ማንኛውም ነገር ለመክፈት ቁልፉን ሲጫኑ የዊንደውስ የቢዚ ምልክት እየተሸከረከረች
ዓይንዎ፣ልብዎ፣አናትዎ ተሸከረክሯለች፡፡
ወደፈለጉት ለመድረስ ታክሲ ወይም
ባስ ቢያስፈልጎ ሰልፍ የግድ ይልዎታል፤ ያውም ከተገኘ ነው፡፡
ብእግርዎ ለመጓዝ የግድ ቢሆንብዎም
መንገዱ ሁሉ ተጨናንቆ መሽሎኪያ ያጣሉ፡፡
ምግብ ለማዘጋጀት፣ለመጠጣት፣ሻወር
ለመውሰድ ቢያምርዎ ውሃ ይጠፋቦታል፡፡
የከተማ ኗሪዎች ያለመበራት መኖር
አይችሉም፡፡መብራት የጠፋበት ከተማ የገሃንም ተምሳሌት ነው፡፡የአዲስ አበባ ኗሪ ከሆኑ ግን ይህ ነገር አዲስ አይሆንቦትም፡፡መብራት
ይሄዳል ይመጣል… እንደ ዓይን ይርገበገባል፡፡
ለነዚህ ሁሉ ችግሮች መፍትሔ
የመንግስት ባለስልጣናትን ቢጠይቁ ‹‹ችግሮቹን ከስረ መሰረታቸውን ለማስወገድ ጠንክረን እያሰራን ስለሆነ ኗሪዎች በትእግስት እንዲጠብቁ
እናሳስባለን፡፡›› የሚል ነው የሚያገኙት ምላሽ፡፡የፈለጉትን ነገር በፈለጉት ጊዜ ማከናወን በጣም አስቸጋሪ እየሆነ ነው፡፡
ሁሌም ‹‹እባክዎ ትንሽ ይጠብቁ!››

No comments:
Post a Comment