Tuesday, July 9, 2013

ዜና በግጥም


 በአዲስ አበባ የእምዬ ማማ
በዛሬው ቀን ይህን ተሰማ::

በአዲስ አበባ
ኩማ ወረደ ወጣ ድሪባ
ተደሰታችሁ ሆዳችሁ ባባ?

ኩማ!
ለውሳኔ ሲያቅማማ
በዚሁ ከተማ
ዛሬ ጉድ ተሰማ
በድሪባ ስልጣኑን ተቀማ::

ችራግራችን አያልቅም የኛ ጣጣ
ኩማ ተረማምዶብን ሄደ ድሪባ መጣ
       በዝምታ ብቻ እኛን ሊቀጣ?
ወይስ እሮሮአችን ሰምቶ ለውጥ ሊያመጣ?
ለማንኛውም ቸር እንሰንብት ሰላም አንጣ::

No comments:

Post a Comment