‹‹የደወሉላቸውን ደንበኛ አሁን ማግኘት አይችሉም፤ እባክዎን ትንሽ ቆይተው ይደውሉ››
እችን ፅሑፍ እንድፅፍ ያነሳሳኝ ሪፖርተር የኢትዮ ቴሌኮምን ወቅታዊ አቋም ተንተርሶ በድረ ገፁ ያስነበበው ፅሑፍ ነው።እንደ አገልጋይ ስራተኛ፣እንደ ተገልጋይ ደንበኛና እንደ ዜጋ ሁኘ ስመለከተው በድርጅቱ ወቅታዊ አቋም ደስተኛ አይደለሁም።ትሻልን አሰናብቶ ትብስን እያመጣ የቁልቁል ማደጉ አሳዛኝ ነው።
አንዲት ሃገር እንደ ሃገር እንድትቀጥል የመንገድ ትራንስፖርት፣የመብራት ሃይል፣የውሃና ፈሳሽ አገልግሎትና ቴሌኮምኒኬሽን በጥራት መስፋፋት ወሳኝ ናቸው።መንገድ የደም ስር ነው።ብራት ሃይል ሃገሪትዋ ቆማ እንድትራመድ ያስችላል ሃይል፣ጉልበት ነውና።ውሃ ደም ነው፤ ያለ ደም ህይወት አይኖርም።ቴሌኮምኒኬሽን ደሞ የስው አንደበት እንዲደመጥ የሚያስችል ማለት ነው።ታድያ አንዲት ሃገር የደም ስርዋ ከተበጠሰ፣ራስዋን ችላ ካልቆመች፣ደምዋ ከደርቆ መናገር ካልቻልች እንዴት መቀጠል ትችላለች?
ኢትዮ ቴሌኮም ከመመስርቱ በፊት ዋሃዌና ዜድቲኢ የቴሌ ኔትወርክን በጋራ ያስኬዱት ነበር። የዛን ጊዜ ታድያ ችግር
በተፈጠረ ቁጥር እርሰበርሳቸው በመካሰስ ችግሮች መፍትሔ ሳያገኙ ይቀሩ እንደ ነበር አይካድም።ለዛም ነበር ዋሃዌ
ተባርሮ ዜድቲኢ የቴሌ ኔትወርክ ሙሉ በሙሉ እንዲቆጣጠረው የተደረገው ለዘመናት ያገሉት ሰራተኞችን መባረር ቀጥሎ
የፍራንስ ቴሌኮሞች ቀዳሚው እርምጃ።ለውጥ መጣ መልሱ ላንባቢዎች።
አሁን ደሞ ዋሃዌና ዜድቲኢ የኢትዮ
ቴሌኮም የበላይ ሃላፊዎችን በየፊናቸው እያማለዱ ይገኛሉ። ልክ እንደድሮው የቴሌ ኔትወርክ ለመቀራመትና ችግሮች
ሲከሰቱም እርስበርሳቸው በመጠቋቆም ብቻ የደምበኞች ሮሮ ለማባባስ።ይህ አካሄድ ድሮ ተሞክሮ የከሸፈ ጉዳይ ስለሆነ
ወደ ሌላ ማለፍ ሲገባን እዛው መለወሳችን በጣም ያሳዝናል።
ቴሌ ሊለወጥ የሚችለው በሰራተኞቹ ተማምኖ ጠንክሮ ሲሰራ ብቻ እንጅ የውጭ ድርጅቶችን በመቀያየር አይደለም።
ለስራተኞቹ ተገቢው ክብር መስጠት አለበት።በዘርና በፖለቲካ አመለካከት በመለያየት ስራተኞችን መከፋፈል ለወደፊትም
ቢሆን ዋጋ ሳያስከፍሉት አይቀሩም።አንድ ስራተኛ ያለቃው መልካም ፈቃድ አግኝቶ ቻይና የመሄድ ዕድል ከገጠመው
በየዓመቱ ለስልጠና የሚመላለስው እሱ ይሆናል።አንዴ ዕድል ካላገኘ ግን ያው እስከወድያኛው አያገኝም።ይህ መቀየር
ያለበት ይመስለኛል።
ቴሌ የራሱ የጥናትና ምርምር ማዕከል ሊኖረው የገባል። ያኔ አውራ ችግሮቹን ለይቶ
በማወቅ ዘላቂ መፍትሔዎች ማምጣት ይችላል።ስልጠና ለሚያስፈልጋቸው ሰራተኞቹም ቻይና ሄደው አስፈላጊውን እውቀትና
ክህሎት ሳይገበዩ ተሸራሽረው ብቻ አይመለሱም።ያ የጥናትና ምርምር ማዕከል እንደ ዘመናዊ የማሰልጠኛ ማዕከል ሆኖ
ያገልግላልና።በዛውም የመከላከያው ብረታብረትና ኢንጅኔሪንግ ኮርፖሬሽን እንደሚያደርገው ሁሉ ቴሌም የቴሌኮምኒኬሽን
እቃዎችን በማምረት እንደ ዜድቲኢና ዋሃዌ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳረ የማይሆንበት ምክንያት አይኖርም።
የኔ አስታያየት ይኸው ነው።እርሶስ ምን ይላሉ? ተራው የርሶ ነው፤ ይጠቀሙበት።
No comments:
Post a Comment