Sunday, July 7, 2013

ምንያህል ታማኞች ነን?





የሃገራችን ከፍተኛ የትምህርት ቶቋሞች ሰሙኑን ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ይገኛሉ፡፡ኢነዚህ ተማሪዎች ከቻሉ እውቀታቸውን በተግባር በማዋል የራሳቸው የድርጅት ባለቤት ሊሆኑ ይችላሉ:: ካልሆነ ደሞ በተለያዩ የመንግስትና የግል ድሪጅቶች ተቀጥረው በየወሩ እየተቆነጠረች በምትከፈላቸው ደሞዝ ንሮአቸውን ለመምራት ይገደዳሉ፡፡የራሳቸው ድርጅት መስረተው ንሮአቸውን የሚመሩም ሆነ በድርጅቶች ተቀጥረው በወርሃዊ ደሞዝ ራሳቸውን የሚያስተዳድሩ ወገኖች አንደ ነገር ያስፈልጋቸዋል፤ ታማኝነት፡፡

ታማኝነት በምንከተለው ሃይማኖት፣በምናራምደው የፖለቲካ ስነ ሐሳብ(አይዲዮሎጂ) እና ተወልደን በደግንበት ብሄር አይወሰንም፡፡ሙስና ሃይማኖት፣ የፖለቲካ አስተሳሰብ ወይም ብሄር አይለይም… በእነዚህ ተቋማት እኩል ሲስፋፋ ነው የምናስተውለው፡፡ ሙስና ደሞ ቁጥር አንድ አገር አጥፊ እምነት ማጉደል ነው፡፡ለራሳችን እና ለድርጅታችን ታማኝ ሳንሆን ስንቀር በሙስና፣ወገኖችን በማጉላላት፣በስርቆት ወዘተ እንዘፈቃለን፡፡

እስኪ በ1999 ዓ.ም የመቀለ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ እያለሁ ለመፂሔት አዘጋጆች ክፍል ልክያት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የታተመችው ታሪክና ምሳሌን በአማርኛ የንበቧትና ምንያህል ታማኝ እንደሆኑ እራስዎትን ይፈትሹ፡፡

ድሮ ነው አሉ፡፡የአንድ ደርጅት ስራስኪያጅ የድርጅቱ ታማኝ ሰራተኛ ለማወቅ ፈለገና ለእያንዳንዱ ሰራተኛ ለም አፈር በተመላው ሼንከሎ ውስጥ አንዲት ፍሬ በማኖር ያድላቸዋል፡፡ ከዛም ሁሉንም ሰራተኞች ሰበሰበና ምርጥ ችግኝ ያሳደገው ሰራተኛ የድርጅቱ ልዩ ሽልማት አሸናፊ እንደሚሆን ያነግራቸዋል፡፡


እያንዳንዱ ሰራተኛ ምርጥ ችግኝ ለማሳደግ ሌትተቀን ሲኳትን ከርሟል፡፡በመጨረሻም የተሰጣቸው የቤት ስራ የሚያስረክቡበት ቀን ደረሰና የያዙትን እቃ ይዘው ወደ ስራስኪያጁ ቢሮ ይሄዳሉ፡፡ሁሉንም ሰራተኞች በጣም የሚያማምሩ ችግኞችን ሲያሳድጉ አንደኛው ግን በውሃ የረጠበችና አፈር የሞላች ሼንከሎ ብቻ ያስረክባል፡፡የሚገርመው ደሞ የዓመቱ የድርጅቱ ልዩ ሽልማት አሸናፊው እሱ መሆኑን መበሰሩ ነው፡፡

ሁሉም ሰራተኞች በውሃ የረጠበችና አፈር የሞላች ሼንከሎ ለስራስኪያጁ ያስረከበው ሰራተኛ ለምን ተሸላሚ እንደሆነ ስላልገባቸው ማጉረምረም ጀምሯል፡፡ተወካዮቻቸውን በመምረጥም ስራስኪያጁን ለመጠየቅ ወደ ቢሮው ያመራሉ፡፡ስራስኪያጁ በሰጠው ምክንያት ግን ሁሉም ሰራተኞች በደርጊታቸው አፈሩ፤ ከብቸኛው ተሸላሚ በስተቀር፡፡

ስራስኪያጁ ‹‹ ውድ ሰራተኞች ሆይ፣ የሰጠኋቹ ፍሬዎች ሁሉም የተቆሉ ስለሆኑ ካልተቀየሩ በስተቀር ሊበቅሉ አይችሉም፡፡ እናም በውሃ የረጠበችና አፈር የሞላች ሼንከሎ ያስረከበው ሰራተኛ ተሸላሚ የሆነው በታማኝነቱ ነው፡፡ እናንተ ግን ምርጥ ችግኝ ለማሳደግ ስትሉ የተቆላችዋን ፍሬ በመቀየር ታማኝነታችሁን አጉድላችኋል፡፡›› በማለት አስረዳቸው ይባላል፡፡

ውድ አንባቢሆይ ምንያህል ታማኝ ኖት? በተሰማሩበት መስክ አብረዎት ሚሰሩ በለደረቦችዎስ ምንያህል ታማኞች ናቸው? አስተያየትዎን ያጋሩኝ፡፡

No comments:

Post a Comment