Friday, July 19, 2013

ሐምሌና የህይወቴ ወሳኝ ምዕራፎች




የተወለድኩባት ወር ጥር ብትሆንም ከሐምሌ ጋር ግን ላወዳድራት አልችልም፡፡ሐምሌ የህይወቴ በጣም ትላልቅ ምዕራፎች የተከናወኑባት ወር ነች፡፡

ሐምሌ 8 ቀን 1999 ዓ.ም ከመቐለ ዩኒቨርሲቲ በድግሪ ስመረቅ በደስታ አልቂሻለሁ፡፡ያኔ በጣም ያመኝ ስለ ነበር እንዳያስተኘኝና ትምህርቴን እንዳላቋርጥ እፈራ ስለነበር በሰላም ተመርቄ ያለምንም ዓይነት መንከራተት ወደ ስራ ዓለም በመቀላቀሌ ደስታየ እጥፍ ድርብ ነበር፡፡ያዓመት ከድህነትና ከበሽታ ባንዴ ነፃ የወጣሁበት ጊዜ ስለነበር የዩኒቨርሲቲ ቆይታየ የመጨረሻ ቃል(last word) “Thanks God, hardship has gone!”(ተመስገን ጌታየ፣ችግር ተሰናበተች!) የሚል እንዲሆን በወሰንኩት መሰረት በመመረቅያ መፅሔታችን ታትሞ እንደ ማስታወሻ እያገለገለኝ ይገኛል፡፡የህይወቴ ሁለተኛው ወሳኝ ምዕራፍ!!!

ሐምሌ 12 ቀን 2004 ዓ.ም ልክ የዛሬ ዓመት ከውድ እጮኛየ(ክብርት ባለቤቴ) ደስታ አብርሃ ጋር ቃል ኪዳን ያሰርንበት ቀን ነው፡፡ብቸኝነት ደህና ሁኚ ብዬ እስከወድያኛው ያሰናበትኩበት ቀን፡፡ብቸኝነት ብቻም አይደለም ማሕበራዊ ብቃቴን(social maturity) ያስመሰከርኩበት ቀን ነበር፡፡ከሰው ጋር ተቻችሎ፣ተስማምቶ፣በመደማመጥ፣በመተሳሰብ አብሮ መኖር የችል መሆኔን ያስመሰከርኩበት ቀን፡፡እስከ ህልፈተ ሞቴ ድረስ ቃሌን ጠብቄ ለመኖር ቃልኪዳን የገባሁበት እጅግ በጣም ትልቅ ቀን፡፡አምላክ ይመስገን ይሀው አንድ ዓመት ሆኖኛል፡፡




የሰው ልጅ ተወልዶ አድጎ ከዚህ ዓለም በሞት እስኪሰናበት ድረስ ሶስት የዕድገት ምዕራፎች ይሻገራል፡፡የመጀመርያው የጥገኝነት(dependence stage) ጊዜ ነው፤ በአብዛኛው ጊዜ ከ18 ዓመት በፊት ያለው የዕድሜ ደረጃ ያጠቃልላል፡፡በዚህ ጊዜ የሌሎች እርዳታ የግድ ያስፈልገናል፡፡ካልሆነ ግን ህይወት ከልክ በላይ ፈታኝ ትሆንበናለች፤ችግሩ ላቅ ሲልም በለጋ ዕድሜችን በሞት ልንቀጭ እንችላለን፡፡


ሁለተኛው (independence stage) የሚባል ሲሆን ለዓቅመ አዳም(ሄዋን) የምንደርስበትና ራሳችን ችለን የምንኖርበት ምዕራፍ ነው፡፡በዚህ ምዕራፍ ከማንኛው የቤተሰብ ጥገኝነት ተላቅቀን ራሳችን ካልቻልን የማህበረሰባችን መጠቋቆምያ መሆን እንጀምራለን፡፡ሰለዚህ በዚሁ ምዕራፍ የግድ ራሳችን መቻል የግድ ይለናል፤ወደድንም ጠላንም፡፡


ራስን መቻል ብቻ ግን በቂ አይደለም፡፡ሌላ በጣም የላቀ ሶስተኛ ምዕራፍ አለ ይለና ዶክተር ስቴፈን ኮቨይ(The Seven Habbits of Highly Effective People የሚባል ተወዳጅ መፅሐፍ ደራሲ)፡፡ተቻችሎ መኖር ወይም ማሕበራዊ ብቃት (interdependence stage or social maturity) የሚባል የሰው ልጅ የመጨረሻ የዕድገት ደረጃ መኖሩን በማውሳት፡፡በዚህ ምዕራፍ ሁለት ራሳቸው ችለው መኖር የሚችሉ ሰዎች በመጣመር(በትዳር በቢዝነስ ወዘተ) እርሰ በርስ እየተረዳዱ አብረው የኖራሉ፡፡መቻቻል፤መረዳዳት፣መደማመጥ የግድ የሚልበት የዕድገት ደረጃ ነው፡፡እናም ለዛ ነው ማሕበራዊ ብቃቴን ያስመሰከርኩበት ቀን ነው ያልኩት፡፡


 ልባለፈው ቅዳሜ(ከሁለት ሳምንት በፊት) ደሞ ውዷ የንሮ አጋሬ(ባለቤቴ) ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጀመርያ ደግሪ የተመረቀችበት ቀን ነበር፡፡ ፡፡የሐምሌ ወር ዝናብ ተከትሎ የሚመጡ ነገሮች(ጭቃ፣ዝናብ፣ብርድ ወዘተ) ለማይወዱ ሰዎች ጨፍጋጋ፣ድብርታም፣ጋግርታም ወዘተ ልትሆን ትችላለች ለኔ ግን ከሌሎች ወራት በበለጠ ታስደስተኛለች…ከላይ በጠቀስኳቸው ምክንያቶችና የገጠር ልጅ በመሆኔ፡፡አርሶ አደሮች የሐምሌ ወር የቤት እንስሶቻቸው ከደረቁ የበጋ ወቅት ተላቅቀው ከሳርቅጠሎች ጋር የሚገናኙበት ወቅት ነው፡፡ምን ይህ ብቻ ዓመት ሙሉ ለፍተው የዓመት ቀለባቸውን የሚያገኙባቸው የእርሻ ማሳዎቻቸውን ለዓይን በሚያማልል ቡቃያ የሚሸፈኑበት ወቅትም ነው፡፡


ውድ አንባቢ ሆይ!የሐምሌ ወር ለኔ ይህን ያህል ልዩ ነች፡፡እርሶስ በጣም የሚወዱት ወር የትኛው ነው?ለምን? ሐሳብዎን ያጋሩኝ፡፡

No comments:

Post a Comment